የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 005/ሽያጭና አገልግሎት/18 ዓ.ም
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- 1ኛ. ለምግብነት የሚውል ጤፍ እና የእህል ብጣሪዎች ሽያጭ ለመጀመርያ ጊዜ
- 2ኛ. የዘር መቋጠርያ ፖሊ ባግ ግዥ ለሶስተኛ ጊዜ
- 3ኛ. የሠራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ
- 4ኛ. ያገለገለ ባለ 100 ኪ/ግ ሚዛን ሽያጭ ለሶስተኛ ጊዜ
በዚሁ መሰረት-
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ሕጋዊ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና የዘመኑን የመንግሥት ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ውድድር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 220 1752/2285/2117 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት
