Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው fibric rope & ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ)፣ መነፅር (የእይታ መሣሪያ) እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 09/2018 .

 

በኢትዮጵያ ጉምሩ ኮሚሽን የአዳማ //ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው fibric rope & ኤሌክትሮኒክስ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኮስሞቲስ፣ ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) መነፅር (የእይታ መሣሪያ) እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ፡ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በአክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የአሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 200-600 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
  4. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡
  5. በግልፅ ጨረታ ላይ የወጡትን ሞተር ሳይክሎች ማንኛውም ዕድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው በቀበሌ መታወቂያ ብቻ የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ፡፡
  6. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባን በተመሰከረለት (CPO) (Customs Adamna Branch) ስም ብቻ ሲፒኦ በማሰራት ያሰሩትንም ... በአካል ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ /ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ ስለሚገኙ ለግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 400 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 /ሶስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ከላይ በተ/ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  11. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
  12. //ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

 

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ///ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

N.B፡- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን ሰነዶች ያላሟላ ተጫራች ቢያሸንፍም ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ሲፒኦ ለመንግሥት ገቢ የሚደረግ እና እቃው በድጋሜ ጨረታ የሚወጣ መሆኑን እንገልፃለን።

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender