የድሬዳዋ ፖሊ ቴክንክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር ለመማር ማስተማር ሂደት የሚያገለግሉ፣ የአውቶሞቲቭ እቃዎች፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ የአይሲቲ እቃዎች፣ ሰርቬይንግ እና ድራፍቲንግ እቃዎች፣ የሆቴል እና ቱሪዝም እቃዎች፣ ውድ ዎርክ ፣ የዴኬር/የህጻናት ማቆያ እቃዎች፣ ቴክስታይል እና ጋርመንት እቃዎችን፣ የትያትሪካል አርት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክንክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር ለመማር ማስተማር ሂደት የሚያገለግሉ፣ የአውቶሞቲቭ እቃዎች፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ የአይሲቲ እቃዎች፣ ሰርቬይንግ እና ድራፍቲንግ እቃዎች፣ የሆቴል እና ቱሪዝም እቃዎች፣ ውድ ዎርክ ፣ የዴኬር/የህጻናት ማቆያ እቃዎች፣ ቴክስታይል እና ጋርመንት እቃዎችን፣ የትያትሪካል አርት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ ከዚህበታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ፣ በሥራው መስክ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና አቅራቢነት የምስርክ ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነዱ 5000.00/አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሠከረ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ የግዥ እና ፋይናንስ ንብረት ዳይሬክቶሬት ክፍል መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታው አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ለተዘረዘሩትን እቃዎች /ለተጫረቱበት/አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከእያንዳንዱ እቃ ናሙና ወይም Sample ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ላሸነፉባቸው እቃዎች የጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ባለው ዝርዝር ሞልተው ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው በኮሌጁ የጨረታ ሳጥን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው ሳጥን የሚዘጋው በ16ኛው ቀን በእለቱ በ3፡30 ሰዓት ሆኖ ጨረታው የሚከፈተው በተመሳሳይ ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በ10 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ኮሌጁ ግቢ ድረስ አምጥተው ያስረክባሉ።
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ሲሞሉ አጠቃላይ ድምር መቀመጥ ይኖርበታል።
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይመ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 025 111 3266 ወይም 025 1111 7602 በደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
