የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የደንብ ልብሶች
- ሎት 2 የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 3. የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች
- ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 5. የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸሮች
- ሎት 6. የቢሮ መጋረጃ፣ የግድግዳ ልባስ ፓኔል፣ አልሙኒየም ፓርቲሽን ፍላይ ውድ እና መስታወት ስራ እና የተለያዩ የበር እና የመሳቢያ ቁልፎች ሲሆኑ
በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው -
ሀ. ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡
ለ. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
ሐ. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚጫረቱበትን ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
መ. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት የስራ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
ሠ. ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
ረ. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን መ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም፣ ፊርማ በማሳረፍ እና ሙሉ አድርሻቸውን በመግለፅ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ሰ. ጨረታው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3:30 ሰዓት ከታሸገ በኋላ በዕለቱ ከቀኑ በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል። ሆኖም 11ኛው ቀን የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
ሸ. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ቀ. ማንኛውም ተጫራች ዋጋውን በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
በ. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115-58-07-15 ወይም 0911-36-05-27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ከፌዴራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት ወደ ልደታ ቤ/ክ በሚውስደው መንገድ ትንሽ ከፍ ብሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ህንፃ 9ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት
