በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የሙዚቃ መሳሪያዎችን፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የፈርኒቸር ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና የተለያዩ ችግኞችን በ2018 በጀት አመት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የሙዚቃ መሳሪያዎችን፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የፈርኒቸር ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና የተለያዩ ችግኞችን በ2018 በጀት አመት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው በመሳተፍ
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና፤ ጨረታ ላይ እንዲሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቀረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም ሲንቄ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 105455116121 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
8. ተጫራቾች ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት። ቴክኒካሉን ያለፉት ተወዳዳሪዎች ፋይናንሻላቸው ይከፈታል።
9. ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ውስጥ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን አስከ አዳማ ከተማ ገንዘብ ዕ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዘው ማቀረብ አለባቸው፡፡
11. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ወጪ ከአዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት፣ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል፡፡
12. ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ ሲሆን፤ 7.5% በክፍያ ጊዜ የሚቀነስ ይሆናል፡፡
13. መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት፡፡
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 022-211-14-42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
