Tender Detail

Tender Details


ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማኀበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EL-MD-2026-281

 

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ /የተ/የግል ማኀበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

 

የሎት ቁጥር

ያገለገሉ ዕቃዎች ዝርዝር

ዕቃው የሚገኝበት ቦታ

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ሲፒኦ (ብር)

ሎት-1

የተለያዩ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ ብረቶችና ቆርቆሮዎች፣ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች፣ የተለያዩ ጎማዎች፣ በርሜሎች፣ የጋዝ ሲሊንደር፣ የተለያዩ እቃዎች

ኮምቦልቻ ምግብ ማቀነባበሪያ፤ ኮምቦልቻ

200,000.00

ሎት-2

ጀነሬተር፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ብረትሊዝ ማሸን አካል፣ የነዳጅ መቅጃ፣ ቦይለር፣ ድሪል፣ ግራይንደር ማሽን እና የተለያዩ እቃዎች

መልጌ ወንዶ አግሮ ፕሮሰሲንግ፤ ወንዶ

200,000.00

ሎት-3

ድሪፕላይኖች፣ የምርት መሰብሰቢያ ሬቶች፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎች እና ፕላስቲኮች

ኤልፎራ ጂቱ እርሻ-ቢሾፍቱ

200,000.00

ሎት-4

ንቃይ ቆርቆሮ፣ የብረት ንች፣ ቱቦ፣ የብረት በር፣ የተለያየ ርዝመት ያላቸው ብረታ ብረቶች፣ በጣውላ የተ ከንች

ድሬዳዋ ቄራ፤ ድሬዳዋ

100,000.00

ሎት-5

ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የተለያዩ ጣውላዎች የተለያዩ የስልክ ቀፎዎች፣ የተለያዩ የጽህፈት  መሣሪያዎች

ጎንደር-ቄራ፤ ጎንደር

100,000.00

 

1.     ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት (VAT) ወይም ተርን ኦቨር ታክስ (TOT) የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2.     ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ (ላምበረት) አካባቢ ከሚገኘው ዋና /ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱ መግዣ ዋጋ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ነው

3.     ተጫራቾች ዋጋ ከመስጠታቸው በፊት ዕቃዎች በሚገኙበት ከተማ በአካል በመገኘት ማየት ይኖርባ ቸዋል

4.     ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለጨረታ ማስከበሪያ /Bid bond/ የሚሆን ብር ከላይ የተገለፀውን በእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው

5.     ለተሸነፉ ተጫራቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

6.     ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በተራ ቁጥር 1 የተገለፁትን ፎርማሊቲዎች በማሟላት በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን መለያ ኮድ (ሎት) እና ቦታ በፓስታው ላይ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡

8.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜ እና እሑድን ሳይጨምር 8 (ስምንት) ቀናት እስከ ቀኑ 725 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

9.     ተጫራቾች በኤልፎራ ዋና /ቤት 4 ፎቅ ግብይት መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታቸውን እንዲያሰገቡ ይደረግና 8ኛው ቀን 730 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፤ በዚሁ እለት 800 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ 8 ፎቅ ጨረታው ይከፈታል፡፡

10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማህበር ዋና /ቤት ግብይት መምሪያ ቢሮ አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ (ላምበረት) አካባቢ በሚገኘው ኤልፎራ ህንፃ 4 ፎቅ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- +251 911-172601/+251 0954495363/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

ፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማኀበር

Save Tender