ዳንኤል ጌታነህ የተመሰከረለት አዲት ድርጅት በመፍረስ ላይ ያለውን አካል ኃ/የተ/የግ/ ማህበር የሆኑትን የሚከተለቱትን ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አሸናፊ ለሚሆኑ ተጫራቾች በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡:
የንብረት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ (Invitation to Bid)
ዳንኤል ጌታነህ የተመሰከረለት አዲት ድርጅት በመፍረስ ላይ ያለውን አካል ኃ/የተ/የግ/ ማህበር የሆኑትን የሚከተለቱትን ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አሸናፊ ለሚሆኑ ተጫራቾች በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡:
ሎት 1 የተጠናቀቁ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች
ሎት 2 ያልተገጣጠሙ እና የተለያዩ የፈርኒቸር ዕቃ ክፍሎች
ሎት 3 የተለያዩ ቆዳዎች፣ እስፖንጅ ኬሚክ ፋይበር እና ጨርቃጨርቅ
ሎት 4 ማጠፊያዎች፣ መቆለፊያዎች እና መገጣጠሚያዎች
ሎት 5 የተለያዩ ብረታብረቶች እና የሻተር መስሪያ ግብአቶች
ሎት 6 የመስሪያ መሳሪያዎች (Tools)
ሎት 7 የተለያዩ የብረታብረት እና የእንጨት ውጤቶች ማምረቻ ማሽኖች
ሎት 8 ኤምዲኤፍ እና የተለያዩ ጣውላዎች
ሎት 9 ኮምፒውተር እና ኤሌክትሮኒክስ
ሎት 10 መኪና
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር አምስት መቶ /500.00/ በመክፈል ሃያ ሁለት አካባቢ ጌትፋም ሆቴል አጠገብ ኢንዲስትሪያል ፕሮጀክቶች አገልግሎት ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ዳንኤል ጌታነህ የተመሰከረለት ኦዲት ድርጅት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ ከሰዓት በኋላ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ሰነዱ ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ድረስ የሚሸጥ ይሆናል፡፡
3. ከላይ የተዘረዘሩት ንብረቶችን በአካል መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የመሸጫ ቀን ከመጠናቀቁ በፊት በተቀመጠው የማስጎብኛ የሥራ ቀናት እና ሰዓት መሰረት በራሳቸው ትራንስፖርት ወይም ድርጅቱ በሚያዘጋጀው ትራንስፖርት በአካል በመቅረብ መመልከት ይችላሉ። / መጎብኘት የሚችሉበትን ቀን ከሁለት ቀናት በፊት አስቀድመው ከዚህ በታች በተገለፀው ስልክ ቁጥር ደውለው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።
4. የጉብኝት ቀናት ሰኔ 15፤ 17 እና 19 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ብቻ ጨረታ ሰነድ ለገዙ አካላት ዱከም በሚገኘው መጋዘን ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች ማሳያ ይሆናል፡፡
5. ለመኪና ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች በራሳቸው ትራንስፖርት ሳሪስ አካባቢ መኪናው በሚገኝበት ቦታ የጨረታ ሰነዳቸውን በማሳየት ከ ሰኔ 13 ፣ ሰኔ 16 እና ሰኔ 18፣ 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ብቻ መመልከት ይችላሉ፡፡
6. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ቀናቶች ከሰኔ 8 እስከ 23 ቀን 2018 ዓ.ም
- ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ
- ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ድረስ እና
- ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ/ም ግን ከጠዋቱ 4፡00 ብቻ ማስገባት ይቻላል፡፡
7. ጨረታው ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለዚሁ ተብሎ በሚዘጋጅ አዳራሽ ይከፈታል። / የጨረታ መክፈቻ ቦታ በውስጥ ማስታወቂያ እና ተጫራቾች በሰነድ ግዢ ወቅት በሚያስመዘግቡት የኢሜል ወይም በስልክ አጭር ፁሁፍ አድራሻው አንዲያውቁት ይደረጋል/፡፡
8. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለመረጃ በስልክ ቁጥር 0920854561 እና 0967138579 መደወል ይችላሉ።
ዳንኤል ጌታነህ የተመሰከረለት ኦዲት ድርጅት
