Tender Detail


አዋሽ ባንከ አ.ማ. ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


ያገ ንብረቶች

የጨረታ ማስታወቂያ

 

አዋሽ ባንከ .. ሲጠቀምባቸው የነበሩትን 10 ተሽከርካሪዎች በሎት (1) እና በሎት (2) (ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች ስካነር፣ ቼክ ስካነር፣ ላፕቶፕ፣ የብር መቁጠሪያ፣ መፈተሻ ማሽን፣ የሂሣብ መደመሪያ፣ የዶላር መፈተሻ ማሽን፣ ፋክስ፣ ፎቶ ኮፒ፣ የውሃ ማጣሪያ፣ ቴሌቭዥን፣ ታይፕራይተር፣ የሙቀት መለኪያ፣ ቬንትሌተር፣ ብሎወር፣ ቴፕ ሪከርደር፣ የተለያዩ ባትሪዎች፣ ዩፒኤስ፣ ስታበላይዘር፣ እሳት ማጥፊያ፣ ወረፋ መጠበቂያ የተለያዩ ወንበሮች ኤም ሼልተር፣ የጥበቃ ቤት፣ ፍራሽ አሉሚኒየም ፓርቲሽን፣ የተለያዩ የማስታወቂያ ምልቶች በሮች፣ መጋረጃ፣ የተለያዩ ንቃይ ቆርቆሮዎች፣ ብረታ ብረቶች የአምፖል ማቀፊያ፣ መስታወት፣ የተለያዩ ገመዶች፣ ካውንተር ዴስክ፣ የተለያዩ ጠረጴዛዎች፣ የኮት መስቀያ፣ የብረት መደርደሪያ፣ የውሃ ማጠራቀሚያ (ሮቶ) የመጽሐፍ መደርደሪያ፣ ፋይሊንግ ካቢኔት፣ ላተራል ፋይሊንግ ካቢኔት፣ እምነበረድ፣ ካርቶን፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እና ጎማዎች) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን-

1.     ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1 ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2018 .. ከቀኑ 400 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ

2.     ተጫራቾች በሎት 1 ላይ ለተገለጹት ተሽከርካሪዎች በባንኩ የተቀመጠውን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንከ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል!

3.     በሎት 2 ላይ ለተዘረዘሩት የቢሮ መገልገያ ንብረቶች ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ንብረት ያቀረቡትን ዋጋ 1/4 የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበርስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣

4.     ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም

5.     የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% ለተሽከርካሪዎቹ የስም ማዘዋወሪያ፣ የተሽከርካሪ የዋጋ ግሥት፣ በጨረታ ዋጋ እና የመንገድ ትራንስፖርት ባለሞያ ግምት መካከል ሊፈጠር የሚችለውን የተ... ልዩነት ገዥ ይሸፍናል

6.     ንብረቶቹን አሸዋ ሜዳ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹን በተመለከተ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ በአካል ቀርበው እና የዙትን የጨረታ ሰነድ በመያዝ በወጣው ፕሮግራም መሠረት መጎብኘት ይችላል።

7.     ጨረታው ሐምሌ 1 ቀን 2018 .. ከጠዋቱ 4:10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1 ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ፍል የቢሮ ቁጥር M-11 ውስጥ ይከፈታል፣ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም

8.     የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል።

9.     ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

10. ስለ ጨረታው አፈጸጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት

ስልክ ቁጥር 0115-303014/0115-576825/0115-303026 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

አዋሽ ባንክ ..

Save Tender