Tender Detail

Tender Details


ዳሽን ባንክ አ.ማ በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባለብት ሁኔታና ቦታ ለሶስተኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::


የጨረታ ማስታወቂያ

የተለያዩ ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ለሶስተኛ ግዜ ለመሸጥ የተዘጋጀ ሽያጭ DB/049/2018

 

ዳሽን ባንክ አ.ማ በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባለብት ሁኔታና ቦታ ለሶስተኛ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

1.     ተጫራ ቄራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 3 ፎት የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል በመምጣት የጨረታውን መረጃ የተጫራ መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፤

2.     ተጫራ ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት የቀረቡ ንብረቶችን በባንኩ መጋዘናችና ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፤

3.     ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ክጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል::

4.     የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው::

5.     ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል::

6.     የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከዳሽን ባንክ .. ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፤ ሆኖም በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ክፍያ በቶሎ ገቢ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ክፍያው በዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች በተዘጋጀ ሲፒኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል::

7.     የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 8 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ 8ኛው ቀን ማለትም ሰኔ 30 ቀን 2018 . ከቀነ 0600 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 0900 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም::

8.     በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 3 /ሶስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 /ሁለት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከባንኩ ጋር ውል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል:: ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ካልፈረሙ ወይም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ግዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል::

9.     ተጫራቾች ያሸነፉብትን ንብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ ውል በፈረሙ 10 የሥራ ቀናት ዉስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::

10. ባንኩ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል::

11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-4655552 011-4706065 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፤

12. ባንኩ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

 

ዳሽን ባንክ አ.ማ.

አዲስ አበባ

.

የእቃው አይነት

መለኪ

ብዛት

1

Managerial Table

በጥቅል

በጥቅል

2

Computer stand and coffee table

በጥቅል

በጥቅል

3

Lowback chair

በጥቅል

በጥቅል

4

Guest chair

በጥቅል

በጥቅል

5

Gun Box

በቁጥር

5

6

Monitor

በቁጥር

25

7

Note Counting Machine

በቁጥር

124

8

Multi-currency Detector

በቁጥር

11

9

Adding Machine

በቁጥር

20

10

Scanner

በቁጥር

49

11

Wall clock

በቁጥር

5

12

Metal Detector

በቁጥር

60

13

Lost and found display

በቁጥር

39

14

Notice Board

በቁጥር

24

15

HP LaserJet Printer

በቁጥር

9

16

Kyocera Printer

በቁጥ

33

 

Save Tender