በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል አላቂ የጽ/መሣሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽ እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና እና የሞተር ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ-01/2019
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል አላቂ የጽ/መሣሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽ እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና እና የሞተር ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው፣ የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱና በፌዴራል ወይም በከልል ገንዘብ ጽ/ቤት በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበትን የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር ዋናውን እና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
2. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ሁሩታ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር10000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በአቅራቢያችሁ የሚገኝ የታወቀ ባንክበከፍያ ማዘዣ ወይም ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ ብር ብቻ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት የሥራ ጉዳይ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. በዋጋ አጻጻፍ ተራ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ የተደለዘው ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡ በተጨማሪም በእርሳስና ቀለም በሚጠጣ ብዕር እንዲሁም ከተሰጠው ቦታ ውጪ የተፃፈ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
6. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 15 የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታውም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15 የሥራ ቀን 6 ሰአት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8 ሰአት ጽ/ቤቱ ለአመቺነቱ በመረጠው ቦታ ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው የእቃ ዋጋዎች /የመወዳደሪያ ሃሳቦች የተጨማሪ ዕሴት ታከስ መካተቱንና አለማካተቱን መግለዕ ይኖርባቸዋል። ይህ ያልተገለጸ ከሆነ፡ የተሰጠው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳከተተ ይወሰዳል::
9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0913395634,0934951727,09 20389358
በአርሲ ዞን የሎዴ ሄጦሳመሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
