Tender Detail

Tender Details


የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂና _ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤ፈርኒቸር፤የጽህፈት መሣሪያዎችን፤የጽዳት እቃዎችን ፤የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ገንዘብ /ቤት 2019 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ /ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂና _ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤ፈርኒቸር፤የጽህፈት መሣሪያዎችን፤የጽዳት እቃዎችን ፤የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:-

* ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብርከፍለው፤ የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና በፌደራል፤በከልል ወይም በዞን ገንዘብ /ቤት ወይም በግዥዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.)ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

* ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች፤ለፅዳት እቃዎች፤ለደንብ ልብስ፤ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በጽ/ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር1000175073578 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ የጽ/ቤቱ የግዢ፤ የንብረትና ፋይናንስ የሥራ ጉዳይ /ቤት ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጨራቶች ከግብር ሰብሳብዉ መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀዉ ለመክፈላቸዉ እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

* ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታውም 16 የሥራ ቀናት ከቀኑ 430 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 500 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ቤቱ ለአመቺነቱ በመረጠው ቦታ ይከፈታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮፈርኒቸር እቃዎች, እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 35000.00 (ሰላሳ አምስት ሺህ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች ፤ለደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 25000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በከፍያ ማዘዣ ወይም ... (C.P.O.) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

+ አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ በወረዳው ውስጥ በሚገኘው ገንዘብ /ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር (0962671408)(0908394066)

ይጠይቁ፡፡

በአርሲ ዞን የሆንቆሎ ዋዋቤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
- Procuring office electronics, furniture, stationery, cleaning supplies, employee uniforms, and vehicle tires for woreda offices for the 2019 budget year. - Issued by the woreda finance office in Arsi Zone, Oromia. - Bid documents cost 300 ETB per document (non-refundable). Submission deadline: 2026-08-19; opening date: 2026-08-20. - Bid bonds: 35,000 ETB per document for electronics, furniture, and stationery; 25,000 ETB per document for cleaning supplies, uniforms, and vehicle tires. - Bidders must have a valid trade license, current tax clearance, supplier registration, VAT registration, and taxpayer ID; the winner must deliver goods at own transport cost to the woreda finance office.
Save Tender