በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ1ኛ የጽ/መሳሪያ 22000 ብር 2ኛ የመኪና እቃ መለዋወጫ 40000 ብር 3ኛ/ የእንስሳት መድሃኒት 20000 ብር 4ኛ የፕሪንተር ቀለም 15000 ብር 5ኛ/ የጽዳት እቃ 8000 ብር 6ኛ ጎማና ከለመዳሪ 15000 ብር 7ኛ ቋሚ የቢሮ እቃ 10000 ብር 8ኛ ህትመት 12000
በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ1ኛ የጽ/መሳሪያ 22000 ብር 2ኛ የመኪና እቃ መለዋወጫ 40000 ብር 3ኛ/ የእንስሳት መድሃኒት 20000 ብር 4ኛ የፕሪንተር ቀለም 15000 ብር 5ኛ/ የጽዳት እቃ 8000 ብር 6ኛ ጎማና ከለመዳሪ 15000 ብር 7ኛ ቋሚ የቢሮ እቃ 10000 ብር 8ኛ ህትመት 12000 ብር 9ኛ የውሃ እቃ 15000 ብር 10ኛ የስፖርት ትጥቅና ማቴሪያል 20000 ብር በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200,000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ የማይመለስ 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተዘረዘረው ሎት የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ /C.PO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቹ በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ዕቃውን በሚ/ወ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች ባሉት ንብረት ክፍል ውስጥ ማድረስ ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ውድድሩ እንደአስፈላጊነቱ በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊሆን ይችላል።
8. ጨረታው ተጫራቾች በአካልም ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 3፡30 ሆኖ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስ/ቁ 09 22 88 42 72 ወይም 09 13 57 44 40 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
