Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር በሰሜን ሸዋ ዞን የእለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ 2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች ፣የኤሌትሮኒከስ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር / ጎማዎች፤ የደንብ ልብስ እና ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር በሰሜን ሸዋ ዞን የእለልቱ ወረዳ ገንዘብ /ቤት 2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች ፣የኤሌትሮኒከስ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር / ጎማዎች፤ የደንብ ልብስ እና ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስሰዚህ የጨረታ መስፈርት የሚያሟሱ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ።

ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ቆይቶ 19/12/2018 . ከቀኑ 600 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከቀኑ 800 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

1.     እቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፋቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፋቃዳቸዉን ያደሱ: ለዚሀም ከሚመለከተው አካል ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል።

2.     በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚለከታቸዉ ፍቃድ ሰጭ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡

3.     በግልም ሆነ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። ዋጋችሁን ስታቀርቡ የአንዱ ዋጋ ሆነ የጠቅላላ ዋጋ ከነ ቫቱ (VAT) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከቫት በፊት የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።

4.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም /brand name/ እና የእቃው ጥራትና ደረጃ መለያው መግለጽ ይኖርባቸዋል።

5.     ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሠነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።

6.     መስሪያ ቤታችን የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።

7.     የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔሲፍኬሽን መሠረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጽም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡

8.     ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ ዓይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል። በነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የጠቅላላ ዋጋ ይወሰዳል።

9.     ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም

10.ለጨረታው የሚቀርበው ሠነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት፡፡

11.አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በፍጹም አይቻልም።

12.ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ ቼክ(CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።

13.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15(ለአስራ አምስት ) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር / በመክፈል አለልቱ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።

14.የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 15 አስራ አምስት የስራ ቀን ቆይቶ 19/12/2018. ከቀኑ 600 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከቀኑ 800 (ስምንት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡

15.የምታቀርቡትን ዕቃዎች አይነት (ናሙናወይም የናሙና ፎቶ በመያዝ ዘወትር በስራ ሠዓት በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ ማምጣት አለባቸው:: ናሙናውን ከወጣው ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔሲፊኬሽን ጋር ማስተያየት ያስፈልጋል። ናሙና የማያቀርብ አቅራቢ ከውድድር ውጪ ይሆናል።

16.ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትከክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።

17./ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

18./ቤቱ ከጠቅላላ ከቫት 7.5% ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

19.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

20.  ከዚህ በላይ በተገለፀው መመሪያ መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈፅሙ ቢቀሩ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር በሰሜን ሸዋ ዞን የአስስቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
- Procuring various permanent and consumable items, cleaning supplies, electronics, vehicle and motor tires, uniforms/clothes, and furniture for the 2019 budget year. - Issued by the Oromia National Regional State, North Shewa Zone, Ethel Tu Woreda Finance Office (as stated in the announcement). - Submission deadline: 19/12/2018 E.C. at 6:00; opening takes place the same day at 8:00. - Bid document price: 300 ETB (non-refundable). Bid bond: 15,000 ETB via bank-confirmed cheque (CPO) or cash. - Bidders must hold a valid trade license, have paid current taxes, be VAT registered, be registered in the suppliers list, and submit product samples.
Save Tender