ሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎች እና ስራዎች በግልፅ ጫረታ ማወዳደር ይፈልጋል
ግልፅ የጫረታ ማስታወቂያ
ሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ለግንባታ የሚውሉ እቃዎች ኤሌክትሮኒክስ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ የስፌት ዋጋ፤ የኮንፒውተር፣ ላፕቶፕ ፎቶ ኮፒ እና ፕሪንተር ጥገና እና የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጥገና የተለያዩ ህትመት እና በከተማችን ውስጥ ለሚደረጉ ፕሮግራሞች የሚውል የዲኮሬሽን ስራና የተለያዩ የምግብ መስተንግዶ የሚውሉ በግልፅ ጫረታ ማወዳደር ይፈልጋል፣
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሞሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኖሮት የታደሰ የንግድ ፈቃድ የያዘና የዘመኑን ግብር የከፈለ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር በአቅራብነት ዝርዝር የተመዘገበና ሰርትፍኬት ያለው፤
3. ተጫራቾች ከወጣቹት ንግድ ስራ ዘርፍ ውጪ የተወዳደረ ተጫራቹ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
4. ለጫረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 150,000 ብር በሲፒኦ በስንቄ ባንክ ብቻ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉት ጨረታውን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10/100 በባንክ ማስያዝ የሚችል፣
5. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ዕቃዎቹን በራሱ ወጪ እስከ ሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል፤
6. መስሪያቤቱ ለሚጠረጥራቸው ና ማጣራት ለሚፈልገው ዕቃ ናሙና ማስቀረብ ይችላል፤
7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛ ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን በዚሁ ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
8. ተጫራቾች የጫረታውን ሰነድ በማይመለስ 1,000 ብር ሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በስንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1051742481211/በቴሌ ብር 518221 ሆፕሬተር አያዲ 615783/181221 ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ትችላላችሁ።
ማሳሰቢያ
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 011 237 0095፣ 09 11 04 56 95፣ 09 13 44 52 27፤ 09 22 20 34 64፤ 09 21 01 07 77 መጠየቅ ትችላላችሁ።
ሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
