የተለያዩ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዥ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2019
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ12 የካራ ጋቢሳ ቀድመ መደበኛ የመጀመረያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019ዓ/ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፣ ስለሆነም ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት መሳተፍ የምትቸሉ መሆኑን እንገልፃለን ፣
በየሎቱ የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮ.ብር
| ሎት1 | የደንብ ልብስ | 6000ብር |
| ሎት2 | አላቂ የቢሮ ዕቃዎች | 3000ብር |
| ሎት3. | የህትመት | 2000ብር |
| ሎት4. | አላቂ የሕከምና ዕቃዎች | 2000ብር |
| ሎት5. | አላቂ የት/ት እቃዎች | 4000ብር |
| ሎት6, | ሌሎች አላቂ ዕቃዎች | 3000ብር |
| ሎት7. | ሌሎች አላቂ መሣሪዎችና መፅሀፍት | 2000ብር |
| ሎት8. | ቋሚ የቢሮ እቃዎች | 10,000ብር |
በጨረታ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ:
- በዘርፋ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግሰት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃቸውንና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የምስከር ወረቀትና ቲን ነበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በተጨማሪም ካሽሬጅስተር ማሽን ደረሰኝ ያላቸው
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት የካራ ጋቢሳ ቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 01 መግዛት ዶችላሉ ስለዚህ በተሰጠው ቀንና ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ሰነዳቸውን አስገብተው ማጠናቀቅ አለባቸው =
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በየሎቱ በተጠቀሰው የዋስትና ማስያዣ ብር መሰረት በባንክ የተመሰከረለት የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒአ/CPO/ ማስያዝ አለባቸው የመወዳደሪያ እቃ ዋጋ ከቫት ጋር ደምረው ህጋዊ ማህተምና ፊርማ አድርገውበት ይላኩልን ፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ኦሪጂናልና ኮፒ አድርገው ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራቾቸ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር ደረጃውን የጠበቀ ናሙና ለት/ቤቱ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ተወዳድረው ካሽነፈበት ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ነው የማቀረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትክከለኛውን እቃ የማምጣት ግዳታ አለባቸው
- ጨረታው የሚታሸገው በ10ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 10፡00ሰዓት ሲሆን በዚሁ እለት10፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል:-
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ/C.P.O/ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፦ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታ ካራ ጋቢሳ የመጀ/ደ/ት/ቤት ከካራ ወደ ጣፎ ሲሄዱ በገደራ ሳራ አምፑል በግራ በኩል ገባብሎ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ሳይት G7 መጨረሻ በስተግራ ታጥፎ 4.5 ኪሜ ገባ ብሎ አዲስ አበባ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር -011-8-68-04-87/0933-73-85-04
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ12 የካራ ጋቢሳ ቀድመ መደበኛ የመጀመረያ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of various goods and services across 8 lots, including uniforms, office supplies, printing, medical items, educational materials, equipment, and books. Bidders must hold valid licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
