የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የቀላል ተሽከርካሪ ጎማዎች ግዥ
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማለትም ፡
1. ሎት-1 የጽህፈት መሣሪያዎችን
2. ሎት -2 የጽዳት ዕቃዎችንና እንዲሁም
3. ሎት-3 የቀላል ተሽከርካሪ ጎማዎችን በብሔራዊ ገልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1- 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የግዥ ፈጻሚው መ/ቤት የተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ 7.5% እና እንዲሁም ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ 3% ቀንሶ በማስቀረት ለሚመለከተው የሚያስተላልፍ ይሆናል።
6. የዕቃና አገልግሎት ግዥ ፍላጎት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በመቅረብና በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጽ/መሣሪያና የጽዳት ዕቃ እንዲሁም የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሽገው በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡01 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
11.የግዥ ፈጻሚ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12.በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመገኘት በፋክስ ቁጥር 011-681-27-36 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 011-681-32-41/ 011-681-6396 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን
ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ
