Supply of Stationery, Cleaning, Furniture and Electronics Items for Sector Offices
የጨረታ ማስታወቅያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ በ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የስቴሽነሪ፣ የፅዳት፣ የፈርኒቸር እና የኤለክትሮኒክስ ዕቃዎች ሕጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዕቃዎችንአገልግሎቶችን ለማቅረብ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
2. የሥራ ተጫራቾች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው
3. ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ (BID SECURITY) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (BANK GAURANTEE) ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለም።
5. ተጨራቾች የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ፅ/ቤት በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ከወንዶ ገነት ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
6. የጨረታው ሰነድ በተጨራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (BID SECURITY) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጂናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል እንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጧቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ጽቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት እያግደውም።
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፍል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. የጨረታው መዝግያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
10. አሽናፊ ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅደመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት
