በጉ/ከ/ከ/መ/04 የጉቶ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተለያዩ የደንብ ልብስ ጨርቆች፣ 2.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ጉ/ሜ/ጤ/ጣ/001/2019
በጉ/ከ/ከ/መ/04 የጉቶ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተለያዩ የደንብ ልብስ ጨርቆች፣ 2. የደንብ ልብስ ስፌት፣ 3. የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ 4. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ 5. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ 6. የእጅ መሳሪያዎች፣ 7. የህትመት ውጤቶች አገልግሎት፣ 8. ፈርኒቸሮች፣ 9. ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ 10. የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች፣ 11. የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ዕቃዎች፣ 12. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ተዛማች ዕቃዎች ጥገና፣ 13. ካፌ አገልግሎት፣ 14. የህክምና ዕቃዎችን፣ 15. የመድሀኒት፣ 16. የላቦራቶሪ ሬኤጀንትን፣ 17. ፓርተሸን የቢሮ ጥገና ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማስራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ፡-
- ከሚገዛው ዕቃ/አገልግሎት ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN No ማቅረብ የሚችሉ፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልጽ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /በዌብሳይት የተመዘገቡ ተጫራቶች ከዌብሳይቱ ላይ ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ሎት1፣ 10,000.00 ብር ሎት2፣ 10,000.00 ብር ሎት3፣ 10,000.00 ሎት4፣ 10,000.00 ሎት5፣ 10,000.00 ሎት6፣ 5,000.00 ሎት7፣ 10,000.00 ሎት8፣ 10,000.00 ሎት9፣ 10,000.00 ሎት10፣ 5,000.00 ብር ሎት11፣ 5,000.00 ብር ሎት12፣ 10,000.00 ብር ሎት13፣ 10,000.00 ብር ሎት14፣ 20,000.00 ብር ሎት15፣ 20,000.00 ብር ሎት16፣ 20,000.00 ብር ሎት17፣ 20,000.00 ብር በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ የሚገባቸው ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን CPO ዋናውን ወይም ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
- ተቋማችን የሚገዛቸውን የአገልግሎት/ዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 በመከፈል 4ኛ ፎቅ ቁጥር 401 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በአንድ ወጥ በታሸገ ፓስታ ኦርጅናልና ኮፒ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ያላካተተ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ የማያቀርብ፣ ስርዝድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀሙ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት በተመረጠው ናሙና ጥራት መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሳጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ ጨርቆች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ የእጅ መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የህክምና ዕቃዎች፣ የህትመት ውጤቶች አገልግሎትን ጥራት ለመለየት የሚያስችልና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በሚገኘው ግዥ ክፍል ናሙና ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ/ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያ እቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፣
- መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ ከውል በፊት 20%/ሀያ ከመቶ/ ጨምሮ ወይም 20% ቀንሶ እና 25% ጨምሮ መግዛት ይችላል፣
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፦ የጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች ባመረቱትና አቅም በጨመሩበት ብቻ ይሳተፋሉ፡፡
አድራሻ፦ ጉቶ ሜዳ ጤና ጣቢያ ኮሪያ ዘማቾች በስተቀኝ 100ሜትር ገባ ብሎ 0116680700
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጉቶ ሜዳ ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Open tender for Guto Meda Health Center to procure and commission various goods and services across 17 lots, including uniforms and fabrics, tailoring, cleaning supplies, office materials, electronics, hand tools, printing, furniture, vehicles, household items, repairs, café services, medical supplies, medicines, lab reagents, and office maintenance. Bidders must hold a valid trade license, TIN, and supplier registration.
