Tender Detail

Tender Details


በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሽሮ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም 1ኛ ዙር ግዥ አገልግሎት የሚውሉ፡-


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሽሮ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም 1ኛ ዙር ግዥ አገልግሎት የሚውሉ፡-

ቁጥር Do1 /2019 ፣ የጽዳት እቃዎች፤ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፊት፤ መዳኒት እና የመዳኒት እቃዎች፤ ቋሚ እቃዎች ፣ ህትመት፤ የጭነትና ትራንስፖርት አገልግሎት ፤ ጉልበት ፤ የኮምፒተርና የፕሪንተር ጥገና የካፌ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች ለ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመከፈል በሽሮ ሜዳ በሚገኘው ጉ/ከ/ከ/ወ/3 ሽሮ ሜዳ ጤና ጣቢያ ገንዘብ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ሆኖ በሚመለከተው ሃላፊ ተፈርሞና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን የጨረታ መስከበርያ በእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ለሎት 1--------10,000 ብር (የጽዳት እቃዎች)

  1. ለሎት2---------15,000 ብር (የጽህፈት መሳሪያዎች),
  2. ሎት 3----------10,000 ብር (የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፊት)
  3. ሎት 4---------25,000 ብር (መዳኒት እና የመዳኒት እቃዎች)
  4. ሎት 5 ------10,000 ብር (ቋሚ ዕቃ)
  5. ለሎት 6--------5,000 ብር (ህትመት)
  6. ለሎት 7-------5000 የጭነት ትራንስፖርት)
  7. ለሎት 8-------5,000 ብር (ጉልበት)
  8. ለሎት 9--------2,000 ብር (ኮምፒዩተር ፕሪንተርና ኮፒ ማሽን ጥገና)
  9. ለሎት10--- 5,000 ብር (የካፌ አገልግሎት)
  10. ተጫራቾች በሎት ከላይ በተገለፀው መሰረት በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  1. መስሪያ ቤቱ ተጫራቾች ከአሸነፉት እቃ ላይ 20% መጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
  2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዚያው እለት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በቀጣይ ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናስ ከፍል ቁጥር 50 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመንግስት ሥራ የማይኖርበት በመንግስት መገናኛ ብዙሃን በመግለፅ የተረጋገጠ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  3. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተመስርቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
  4. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በውላቸው መሠረት ሙሉ በሙሉ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
  5. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ተጫራቾች እስፔስፊኬሽን ከቀረበባቸው እቃዎች ውጪ ላሉት በሙሉ ናሙና (Sample) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዳችሁን ዋናውንና ኮፒውን ማስገባት ይጠበቅባችኃል፡፡
  8. የሞላችሁበትን የጨረታ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 50 ቀርባችሁ ማስገባት አለባችሁ፡፡
  9. ጨረታውን ያሸነፈ በራሱ ትራንስፖርት የሚያቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ስተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011- 1236663/62

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሽሮ ሜዳ ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Open tender for Shiro Meda Health Center in Gulele Sub-city, District 3, for 2019 first-round procurement of cleaning supplies, office materials, uniforms, medicines, equipment, printing, transport, labor, computer/printer repair, and café services across 10 lots. Bidders need renewed licenses, tax compliance, and VAT registration.
Save Tender