የኢሉ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመስሪያ ቤቱ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎችን፤ የደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የመኪና ጎማ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
የኢሉ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመስሪያ ቤቱ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎችን፤ የደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የመኪና ጎማ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 400 በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በኢሉ ወረዳ ፍ/ቤት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ቢድ ቦንድ ብር 5000 /አምስት ሺህ/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ፤ ቼክ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በተሸገ እንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ ለተዘጋጀው ሳጥን በ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው ቦታ ይከፈታል፡፡
- በተራ ቁጥር 4 እና 5 ላይ የተገለፀው ቀን ዕለቱ የበዓል ቀን ላይ ከዋለ ወይም ዕለቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሣሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ባሉ ቀናቶች በኢሉ ወረዳ ፍርድ ቤት ታጂ ከተማ ከአ/አ 55 ኪ/ሜትር ላይ በራሱ መጓጓዣ ዕቃዎቹን አቅርቦ ማስረከብ ይኖረበታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው መሠረት ዕቃዎቹን ሙሉ ከአስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 0113390051/0938620309
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የኢሉ ወረዳ ፍ/ቤት
✨ messages.ai_summary
The Ilu District Court seeks bids to procure office supplies, cleaning materials, uniforms, electronics, vehicle tires, and fixed office furniture. Bidders must hold a valid, renewed business license and deliver items to Taj Town using their own transport.
