በሸገር ከተማ የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ፈርኒቸሮችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ሕጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመርያ መሠረት ጨረታውን እንድትካፈሉ ተጋብዘዋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂይ
ጨረታ ቁጥር፡_002/2019
በሸገር ከተማ የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ፈርኒቸሮችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ሕጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመርያ መሠረት ጨረታውን እንድትካፈሉ ተጋብዘዋል።
የጨረታ ዝርዝር ሁኔታዎች፡-
የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1054472341218 ገቢ በማድረግ ገንዘብ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ስሊፕ በመያዝ ወደ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመሄድ የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ከመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የተጫራቾ ግዴታዎች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN No ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
5. በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
6. ማንኛውም ተጫራች በባንክ የተመሰከረ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል።
7. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ወጪ ጭኖ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመውሰድ ገቢ ማድረግ የሚችል።
8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ የሚያቀርበው ዕቃ በሙሉ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብ የሚችል።
9. ማንኛውም ተጫራች ባለው ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ዘርፍ ላይ ተመስርቶ የጨረታ ሰነድ የተዘጋጃው በሎት ስለሆነ በፈለገው የሎት ዓይነት ብቻ መርጦ ወይምሙሉውን ሎት ገዝቶ መወዳደር የሚችል።
10. አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በትክክል በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የመንግሥት የሥራ ቀናት ውስጥ በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላል።
12. ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፦ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
