በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር በሻሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ/ም በጀት አመት የ1ኛ ዙር ጥቅል ጨረታ ግዢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር በሻሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ/ም በጀት አመት የ1ኛ ዙር ጥቅል ጨረታ ግዢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሎት ዝርዝር ፦ ሎት 1 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ፣ ሎት 3 የትምህት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 ህክምና ዕቃዎች፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ ሎት 7 የፈርኒቸር እቃዎች ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
1. ህጋዊ የሆነና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑንግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ላይየተመዘገቡ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ። እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
2. ተወዳዳሪው የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።
3. ተጫራቹ የንግድ ሰርተፍኬት ከግብር ሰብሳቢ ክፍል የተሰጠውን ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ በየሎቱ 1% ተደርጎ የተሰላ ብር ለሎት1 =27000፣ ለሎት 2 =23104 ለሎት 3 =10000 ፣ለሎት4 =29000፣ ለሎት 5= 3000፣ ለሎት 6= 34500 እና ሎት 7= 34000 ብር ህጋዊነቱ ከታወቀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) እንደሚወዳደሩበት ሎት ብዛት አንድ ላይም ሆነ ለየብቻ ማሰራት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በሻሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስና ግዢ ክፍል ቢሮቁጥር 03 በመቅረብ መግዛት ትችላላቹ።
6. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ማስረጃዎችን ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
7. ጨረታው በወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ላይ የጨረታው ሳጥን ይታሸጋል የጨረታ ሰጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውንም የተጫራቾች ማስረጃ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።
8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን ላይ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
9. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት ማድረግ ይኖርባቸዋል።
10. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም ሌሎች አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ሳንፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
12. ለተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአንስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የተደራጁ ተጫራቾች ህጋዊ ማስረጃ ካደራጃቸው ተቋም በበላይ ሀላፊ ወይም በፅህፈት ቤት ሀላፊ የተፈረመ የትብብር ደብዳቤ ኦርጅናል በማምጣት ያለ ክፍያ ይሰጣቸዋል።
13. ለአነስተኛና ጥቃቅን ተጫራቾች 3% ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል። ነገርግን የእቃውን 35% ወይም ከዛ በላይ ከአገር ውስጥ የታከለ እሴት መሆኑን የሚያስረዳ በተመለከተ በኦዲተር የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
14. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት።
15. መ/ቤ/ቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡_ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ስሙ ሰሚት ፍርድ ቤት ወደ ቀኝ ገባ ብሎ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 668-1243 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር በሻሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
