Tender Detail

Tender Details


በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 03/ት/ፅ/ቤት የፈለገህይወት የቅ/አ/ናመካከ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ ልዩ ልዩ አስፈላጊ የሚሆኑ ማቴሪያሎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ሎት1.


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 03/ት/ፅ/ቤት የፈለገህይወት የቅ/አ/ናመካከ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ ልዩ ልዩ አስፈላጊ የሚሆኑ ማቴሪያሎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ሎት1. የስራ ልብስ እና የስራ ልብስ ስፌት ሎት2. አላቂ የቢሮ እቃዎችና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት3. አላቂ የፅዳት እቃዎች ሎት 4. አላቂ የትምህርት እቃዎችና አላቂ የህከምና እቃዎች ሎት5. ቋሚ እቃዎች (የአይቲ እቃዎችና የቢሮ እቃዎች) ሎት6. የህትመት ስራዎች ሎት7. የተለያዩ የጥገና ስራዎች (የማሽነሪ ጥገና የአይቲ እቃዎች) ሎት8. ግማሽ ሊትር ውሃ፤ ኩኪስ እና ቆሎ ሎት9. የቢሮ ማስዋቢያ እቃዎች፤ ሽልማት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል:: ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ሎቶችና የጨረታ ኮዶች ላይ መወዳደር ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች (አመልካቾች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይፈልጋሉ::

ተ.ቁ የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መግለጫ የግዥው ምድብ የግዥው ሎት ምድብ ምድብ ፋይናንስ መደብ የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒዮ/መጠን ብር
1 የስራ ልብስ እና የስራ ልብስ ስፌት ዕቃ/አገልግሎት ሎት 1 መደበኛ በጀት 16,000.00 1%
2 አላቂ የቢሮ እቃዎችና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ዕቃ ሎት2 መደበኛ በጀት 11,500.00 1%
3 አላቂ የፅዳት እቃዎች ዕቃ ሎት3 መደበኛ በጀት 15,000.00 2%
4 አላቂ የትምህርት እቃዎችና አላቂ የህከምና እቃዎች ዕቃ ሎት4 መደበኛ በጀት 17,000.00 2%
5 ቋሚ እቃዎች (የአይቲ እቃዎችና የቢሮ እቃዎች) ዕቃ ሎት5 መደበኛ በጀት 19,500.00 1%
6 የህትመት ስራዎች አገልግሎት ሎት6 መደበኛ በጀት ውስጥ ገቢ 9,800.00 2%
7 የተለያዩ ጥገናዎች ስራዎች (የማሽነሪ ጥገና የአይቲ እቃዎች) አገልግሎት ሎት7 መደበኛ በጀት 5,000.00 2%
8 ግማሽ ሊትር ውሃ እና ቆሎ፡ ኩኪስ ዕቃ ሎት8 መደበኛ በጀት 2,000.00 2%
9 የቢሮ ማስዋቢያ እቃዎች፤ ሽልማት ዕቃ ሎት9 መደበኛ በጀት 2,000.00 2%
  1. በዘርፉ ህጋዊ ታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከሊራንስ እና ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው:: በአቅራቢ ሊስት መመዝገባቸውን /ዌብሳይት ድርጅት ዝርዝር የተመዘገበ
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ ግዥ ከፍል በቀጥታ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ሰጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በራሳችሁ የምታመርቱት ምርት ብቻ ደብዳቤ በመያዝ መሳተፍ እንጂ ለሌሎች እቃዎች ላይ ለምትወዳደሩበት እቃዎች እንደማንኛውም ተጫራች ማስያዥና የጨረታ ሰነድ ገዝታቹሁ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን፡፡
  4. ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸው ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ የተሸጠውን የጨረታ ሰነድ ተመላሽ መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ትምህርት ቤቱ (ድርጅቱ) ድረስ በማምጣት ያስረከባል፡፡
  6. በጨረታው ላይ ለምትወዳደሩባቸው እቃዎች የእቃዎቹን ናሙና ጨርቅ በጣቃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት አለባችሁ:: ሻጭ ድርጅት ለሚያቀርቡት ዕቃ ህጋዊ ዋስትና ለአንድ ዓመት ጋራንቲ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነዳቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግ በታሸገ ፖስታ ስምና ፊርማ እና የድርጅታቸውን ማህተብ እና ሙሉ አድራሻ በመግለፅ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በክኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ቀኑ የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ፖስታው ተሟልቶ እስከ ተገኘ ድረስ ጨረታውን አያስተጓጉለውም፡፡ አቅራቢ ድርጅት በጥፋተኝነት ያልታገደ መሆን አለበት፡፡ በተጫራቾች መሙላት ያለበት ከፍል መሞላት ይኖርበታል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ውሉን ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) ዋስትና ማስያዝ አለባቸው::
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊው በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሑፍ በተገለፀ በ7 ቀናት ውስጥ ውሉን መዋዋል ይጠበቅበታል:: የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒዩ 0.5-2% ማስያዝ አለባቸው፡፡

አድራሻ፦ ከሰባተኛ ወደ አብነት የሚወስደው መንገድ ከቶታል ዝቅብሎ በቀድሞው በወረዳ 02 ቅያስ ባለው ገባ ብሎ ስልክ ቁጥር 011-827-98-95/

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 03/ት/ጽ/ቤት የፈለገህይወት የቅ/አ/ናመካከ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for purchasing various materials for the 2019 academic year, divided into 9 lots: work clothes and tailoring, office supplies, cleaning items, educational and health supplies, IT and office equipment, printing services, repair services, water/cookies/corn, and office decoration/awards. Bidders must have valid licenses, tax clearance, VAT registration, and TIN.
Save Tender