Tender Detail

Tender Details

  • Company በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ገላን ኮንደሚንየም ፓስ እስቴሽን ወረድ ብሎዳዊት ህንፃ, Phone: 0900046299
  • Website
  • Deadline07 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 300 /ሦስት መቶ ብር/
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 ፋይናንስ /ቤት በግልጽ ጨረታ የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Ø ሎት 1 የደንብ ልብስ

Ø ሎት 2 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች

Ø ሎት 3. የጽዳት እቃዎች

Ø ሎት 4 አላቂ የቢሮ እቃዎች

በዚህም መሰረት መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

1.     በዘርፉ የተሰማራችሁ የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ክፍያ ሰርተፍኬት፤ የቲን መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.     የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብርበመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት 230-1130 ሰዓት በአቃቂ ቃሊቲ /ከተማ ገላን ኮንዶሚኒየም ባስ እስቴሽን ወረድ ብሎ ወረዳ 12 ፋይናንስ /ቤት 3 ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 3-03 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

3.     የጨረታ ማስከበሪያ ለደንብ ልብስ ሃምሳ ሺህ /50,000/ ብር፣ ለአላቂ የፅሕፈት መሣሪያ እቃዎች አርባ ሺህ /40,000/ ብር፣ ለፅዳት እቃዎች ሃያ ሺህ /20,000 /ብር፣ ለአላቂ የቢሮ እቃዎች ሃያ ሺህ /20,000/ ብር ሲፒኦ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው ሲታወቅ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.     ጥቃቅን እና አነስተኛ ካደራጃችሁ አካል መረጃ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

5.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት በቢሮው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በዛው እለት ከጠዋቱ 430 ይከፈታል።

6.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።

7.     ተጫራቾች አሽናፊ መሆናቸው ከተገለጸ ከሰባት /7/ ቀናት በኋላ ቀርቦ ውል መፈጸም አለባቸው፡፡ በዚህ ጨረታ መመሪያ ያልተካተቱ ሌሎች ሁኔታዎች በሀገሪቱ ሕግና ደንብ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የእቃ ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 3/2002 መሰረት የሚታይ ይሆናል።

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡አቃቂ ቃሊቲ ገላን ኮንደምንየም ባስ እስቴሽን ወረድ ብሎ ዳዊት ሕንፃ

ለተጨማሪ መረጃ  በስልክ ቁጥር 0992735325/ 0910887122 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 ፋይናንስ /ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of uniforms, office supplies, cleaning items, and office furniture across four lots. Bidders must hold valid trade licenses and relevant certificates. Samples required before bid opening.
Save Tender