በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፊሊጶስ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም የስራ ዘመን የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም፡-
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፊሊጶስ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም የስራ ዘመን የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም፡-
- ሎት 1. የፅህፈት እቃዎች ግዥ
- ሎት 2. የፅዳት እቃዎች ግዥ
- ሎት 3. የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
- ሎት 5. የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ
- ሎት 6. የህትመት ግዥ
- ሎት 7. የጭነት አገልግሎት ግዥ
- ሎት 8. የችግኝ ግዥ
- ሎት 9. የመፅሀፍት ግዥ
ከላይ በሎት የተዘረዘሩት እቃዎች ድርጅታችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
- የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በአዋጁ መሠረት የተቋቋሙ አምራች በሆኑበት ዘርፍ ብቻ ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች መደበኛውን የጨረታ ሰነድ ሳይገነጠል በሙሉ ተመላሽ ማድረግ አለባቸው
- ተጫራቾች ከጨረታ መዝጊያ ሶስት (3) ቀናት በፊት ቀደም ብለው ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- እስከ መስሪያ ቤቱ ድረስ ለማምጣት ቀላል እና ለማንቀሳቀስ ከባድ ያልሆኑ እቃዎች ሳምፕል በአካል መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በፎቶ የሚቀርቡ ናሙናዎች ከለር ፕሪንት ሆነው ስለ እቃው ግልጽ የሆነ የፅሁፍ ማብራሪያ (እስፔሲፊኬሽን) ያለው መሆን አለበት።
- ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO፣ ሎት 1፣ 10,000 (አስር ሺ ብር)፣ ሎት 2፣ 10,000 (አስር ሺ ብር)፣ ሎት 3፣ 25,000 (ሀያ አምስት ሺ ብር)፣ ሎት 4፣ 40,000 (አርባ ሺ ብር)፣ ሎት 5፣ 25,000 (ሀያ አምስት ሺ ብር)፣ ሎት 6፣ 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር)፣ ሎት 7፣ 5,000 (አምስት ሺ ብር)፣ ሎት 8፣ 10,000 (አስር ሺ ብር)፣ ሎት 9፣ 5,000 (አምስት ሺ ብር) ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ 4ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 68 መጥተው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ከ፡ 00 ሰዓት ብቻ የመጫረቻ ሰነዳቸውን መስሪያ ቤቱ ለዚህ አገልግሎት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በ11ኛው ቀን የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው በክፍት ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጨረታ ኮሚቴ እና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ታሽጎ በዛው እለት ወዲያውኑ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ በጨረታ ከቀረበው የእቃ ብዛት እስከ 20% መቀነስም ሆነ መጨመር ይችላል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ኦርደር ከተሰጠው ከሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ የጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ በማቅረብ ውል መግባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ መደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት፣ ፋይናንሻል ኦርጂናልና ፋይናንሻል ኮፒ፣ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ፣ ለየብቻ በካኪ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም አድርገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት እስከ መስሪያ ቤት የሚያቀርብ ይሆናል።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈው እቃ የውል ማስከበሪያ 10% (አስር ፐርሰንት) አስይዞ ውል ሳይገባ እቃ ወደ መስሪያ ቤት ማምጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ኦርደር ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
አድራሻ፡- ከኮልፈ ስጠና ተራ ወደ ሱሚ-ሜዳ በሚወስደው መንገድ / ፊሊጶስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ሰፊት አንገኛለን። ስ.ቁ፡- 011-2-73-92-45
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፊሊጶስ ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Open tender for the supply of goods across nine lots: office supplies, cleaning items, uniforms, electronics, furniture, printing, transport services, seedlings, and books. Eligible bidders must hold valid business registration, TIN, renewed license, tax clearance, VAT registration, and Ministry of Finance certificate. Samples required three days before closing.
