በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የሻውል ደማ ቅድመ እንደኛ፤ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 2019ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የሻውል ደማ ቅድመ እንደኛ፤ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 2019ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ለግዥ የቀረቡ ዕቃዎችና የጨረታ ማስከበሪያ CPO በየሎቱ ቀርበዋል፡፡
| ሎት 1. | የደንብ ልብስ እና የእስፖርት ትጥቅ ስፌት | CPO 6,900.00 (0.5%) |
| ሎት 2. | አላቂ የፅዳት እቃዎች ግዥ | CPO 3,800.00 (0.5%) |
| ሎት 3. | አላቂ የጽህፈት እቃዎች ግዥ | CPO 1,340 (0.5%) |
| ሎት 4. | የትምህርት መርጃ ግዥ | CPO 1,025.00 (0.5%) |
| ሎት 5. | ቋሚ ዕቃዎች ግዥ | CPO 9,000.00 (0.5%) |
| ሎት 6. | የህከምና መዳኃኒቶች | CPO 1,100.00 (2%) |
| ሎት 7. | ሰፕላንና ማሽነሪ እድሳት | CPO 1,100.00 (2%) |
| ሎት 8. | ለህንፃና ቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች እድሳት ጥገና | CPO 6,911.00 (0.2%) |
| ሎት 9. | የጥገና ዕቃዎች | CPO 1,727.75 (0.5%) |
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት /ቫት/ የተመዘገበበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/መቶ ብር/ መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡
- የመወዳደሪያ መነሻ ሒሳብ ከነቫቱ ዋጋውን በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት የዕቃ አይነት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ላላቀረቡት ናሙና መወዳደር አይችሉም፡፡ ናሙና የማቅረቢያ ጊዜ ጨረታው ሳይከፈት 3 ሦስት ተከታታይ የስራ ቀናት ሲቀረው ይሆናል፡፡ ናሙና በማያቀርቡ እቃዎች ላይ በፎቶ ግራፍ ማቅረብ ይገባል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይናንስ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታፅፋ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማሩበትን የንግድ ስራ መስክ ዘርፍ የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለዚሁም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ከጠዋቱ ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በሲፒኦ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-2-29-11-05 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ አድራሻ ወደ ከሰባተኛ ወደ አማኑኤል የሚወስድበት መንገድ ገባ ብሎ፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሻውል ደማ ቅድመ አንደኛ፤ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for purchasing goods across 9 lots: uniforms/sportswear, cleaning supplies, office supplies, educational materials, fixed assets, medicines, spare parts/machinery repair, building maintenance, and repair items. Bidders need valid trade license, VAT registration, and must submit samples.
