የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ መኪናዎች፣ ያገለገለ ዶዘር፣ ያገለገለ ሎቤድ ተሳቢ፣ ሞተር ሳይክሎች፣ በተለያዩ ሁኔታ የተቃጠሉ መኪናዎች፣ የመኪና መለዋወጫና ቁርጥራጭ ብረታብረቶች ፣ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ ጄኔሬተሮች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የመኪና ባትሪዎች ፣ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ባህር ዛፎች፣ የጽድ ዛፎች እና የግራር ዛፎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 30/2017
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ መኪናዎች፣ ያገለገለ ዶዘር፣ ያገለገለ ሎቤድ ተሳቢ፣ ሞተር ሳይክሎች፣ በተለያዩ ሁኔታ የተቃጠሉ መኪናዎች፣ የመኪና መለዋወጫና ቁርጥራጭ ብረታብረቶች ፣ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ ጄኔሬተሮች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የመኪና ባትሪዎች ፣ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ባህር ዛፎች፣ የጽድ ዛፎች እና የግራር ዛፎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ምድብ አንድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ፤ ላገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ፣ ጀኔሬተሮች ፣ የመኪና ጎማዎች ፣ የመኪና ባትሪዎች ፣ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ባህርዛፎች ፤ የጽድ ዛፎች እና ለግራር ዛፎች እንደየ ምድባቸው የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በቤ/ጉ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 30 በመቅረብ ሰነዶችን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ማስታወቂያው በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ⁄ ለሚወዳደሩበት ንብረቶች የሚጫረቱበትን የገንዘብ መጠን የጠቅላላ ዋጋ 20% በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በቤ/ጉ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ ስም የተሰራ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ቢሮ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ከጠቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡
- 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ከጨረታው ጋር በተያያዘ አለመግባባት ቢፈጠር ጉዳዩ የሚፈታው በክልሉ ውስጥ ሆኖ በክልሉ ህገ መንግስት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በሞባይል ቁጥር 0910932774 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
አሶሳ
