Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ጥራታቸውን የጠበቁ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

የቅድሚያ ብቃት ማረጋገጫ ማጣሪያ ግልጨረታ ቁጥር ግጨ /ቅብማማ01/2017

 

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሀገሪቷ ቁልፍ የመሰረተ ልማት ፍላጎቶች በሆኑት በመንገድና ድልድይ፣ በው ኢነርጂ፤ በህንጻና ከተማ ልማት እንዲሁም በሌሎች የሲቪል ምህንድስና ሥራዎች በሚፈለገው ጊዜ፣ መጠንና ጥራት በማቅረብ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ በዲዛይንና በግንባታ ሥራዎች መስክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው:: ከዚህ በተጨማሪ በጂኦቴክኒካልና ጂኦሎጂካል ሥራዎች፣ በቅየሳ፣ በላቦራቶሪ ምርመራና ሥልጠና መስ አገልግሎቶችን እየሰጠ ሲሆን፤ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በግብዓትነት የሚያስፈልጉ ጥራታቸውን የጠበቁ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በቅድመ ብቃት ማረጋገጫ ማጣሪያ ግልጽ ጨረታ መሰረት በመለየት በአቅራቢነት በመመዝገብ በወቅቱና በጥራት ዕቃዎችን ሊያቀርቡ የሚችሉትንና በቀጣይና በዘላቂነት ከኮርፖሬሽኑ ጋር አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ ድርጅቶችን በመለየትና በማወዳደር ለቀጣይ ውድድር መጋበዝ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:-

  1. ተመዝጋቢዎች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስርወረቀት የሚያቀርቡ፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ እንደዚሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና መመዝገባቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  2. ተመዝጋቢዎች የድርጅታቸውን አሁናዊ ገፅታ የሚያሳይ ፕሮፋይል፣ የሥራ አፈጻጸምን የሚገልፅ ማስረጃ፣ በኦዲት የተረጋገጠ የትርፍ እና ኪሳራ የሂሳብ መግለጫ የቅርብ ዓመታት፣ ከጥራት (ISO Certificate) እና ብቃት ጋር የተያያዙ ሌሎች መረጃዎቸ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  3. ተወዳዳሪዎች የሚመዘገቡባቸው የውድድር ዘርፎች

 

ምድብ

የዕቃው ዝርዝር

1

የሥራ ደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት

2

የጽዳት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች

3

የጽህፈት መገልገያ መሳሪያዎች እና የፕሪንተር ቀለም/ ቶነር

4

የተለያዩ ደረሰኞ ህትመት እና የማስታወቂያና ባነር ሥራ

5

የአውቶሞቢል እና የመስክ ተሽከርካሪ የመለዋወጫ ዕቃዎች

 

  1. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው
  2. ተመዝጋቢዎች ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ዘወትር በሥራ ሰዓት ኮርፖሬሽኑ ያዘጋጀውን ፎርም (ቅጽ) በመውሰድ አስፈላጊውን የድርጅታችሁን መረጃዎች በመሙላት፣ ፊርማና ማኅተም በማድረግ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

ሕንጻ 1 ስራተኛ ፎቅ፡ በኮርፖሬት አገልግሎቶች ቢሮ፣ ኮርፖሬት ግዥ ቡድን

ቦሌ ክፍ ከተማ ወረዳ 05

ስልክ ቁጥር +251 118720722

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

 

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

 

Save Tender