የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ህጋዊ የሆኑና መስፈርት የሚያሟሉ ነጋዴዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የቢሮ ውስጥ ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እንዲሁም የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪ ጎማዎች መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ህጋዊ የሆኑና መስፈርት የሚያሟሉ ነጋዴዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የቢሮ ውስጥ ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እንዲሁም የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪ ጎማዎች መግዛት ይፈልጋል።
መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የ2017 ዓ.ም ግብር ከፍሎ ለ2018 ዓ.ም ንግድ ፈቃዱን ያደሰ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
- የቫት (15%) ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር መዝገብ ላይ የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- በመንግስት ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ያልተከለከለ እና የተከለከለ ከሆነ የጊዜ ገደቡን የጨረሰ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳነዱ የጨረታ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በበደሌ ከተማ ሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1071291641810 ላይ ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በዚህ ማስታወቂያ ላይ ከ 1 - 4 የተዘረዘሩት ማስረጃዎች መኖራቸውን የሚያሳይ በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ በአንድ ፖስታ ውስጥ ታሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መግባት ይኖርባቸዋል።
- የሚገዙ ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት የሚያቀርቡትን ዋጋ ቫትን (15%) ጨምሮ በጥንቃቄ በመሙላት በአንድ ፖስታ ውስጥ ታሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መግባት ይኖርባቸዋል።
- አንድ ተወዳዳሪ ለአንድ ዓይነት ውድድር ሁለት (2) ፖስታ ማስገባት ያለበት ሲሆን የመወዳደሪያ መስፈርቶች ያለበትን ፖስታ የቴክኒክ በማለት እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሞላው የዋጋ መወዳደሪያ ያለበት ፖስታ ላይ የፋይናንስ (financial) በማለት ተለይቶ መጻፍ ይኖርበታል።
- ለማንኛውም አይነት ጨረታ የሚሞላው የመወዳደሪያ ዋጋ ከነቫት መሞላት አለበት፤ በዚሁ መሰረት ቫት (15%) ሳይጨመር የተሞላ ወይም ቫት ያስጨምራል ተብሎ የሚሞላ ዋጋ አናወዳድርም።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ ፈርማውንና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ስርዝ ድልዝ ያለው የቴክኒክም ሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ወጪ ጭኖ እስከ በደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በማምጣት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- የሠራተኞችን ደንብ ልብስ ለማቅረብ የሚወዳደር ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የልብስ ዓይነቶች የሚያሳይ ግልጽ የሆነ ናሙና እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጻፈው የልብስ አይነት በቀረበው ዋጋ በናሙናውም ላይ በግልጽ ተጽፎ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜና ቦታ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በዚሁ መሰረት ሕጋዊ የሆኑና አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ነጋዴ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 01/12/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 የስራ ቀን መካከል የበደሌ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በመሄድ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት በማምጣት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ በመውሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ጨረታው በ22/12/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 047-4-45-23-85 ላይ በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
