የጨረታ መለያ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዥው ዓይነት
ሎት 1 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
ሎት 2 የጽህፈት መሣሪያዎች እና ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 3 የደንብ ልብስ
ሎት 4 የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫዎች
ሎት 5 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በሰራው ዘርፍ ቀጥተኛ እና ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በመሙላት በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።
- ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) በሲፒኦ (CPO) ብቻ በማስያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሪጅን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልተገለጸ ግን ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት ኮፒ እና ኦርጂናል በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡበ ሪጅን ጽ/ቤት በተገለፀው ቀን ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፀው መሰረት ናሙና እንዲቀርብ በተጠየቁት ዕቃዎች ላይ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ ላይ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ሪጅን ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሀዋሳ ቤተሰብ መምሪያ አጠገብ
ስልክ:- 046-221-43-17/046-221-41-40
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት
