Tender Detail

Tender Details


የኦሞ ናዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው መ/ቤቶች የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ፣ እስቴሽነሪ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመንግስት ሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች፣ የመኪና እና የሞተርሳይክል መለዋወጫ ጎማዎች፣ የሕንፃ መሳሪያ እቃዎች፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን በ2018 የበጀት ዓመት አወዳድረን ለመግዛት ስለምንፈልግ የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቶች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ናዳ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ለወረዳው /ቤቶች የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ፣ እስቴሽነሪ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመንግስት ሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች፣ የመኪና እና የሞተርሳይ መለዋወጫ ጎማዎች፣ የሕንፃ መሳሪያ እቃዎች፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን 2018 የበጀት ዓመት አወዳድረን ለመግዛት ስለምንፈልግ የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቶች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

  1. የዘመኑን ንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ፤ የመንግስት ግብር የከፈሉና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑና ተፈላጊ መረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው ከተነገረበት እለት አንስቶ መስሪያ ቤታችን ድረስ በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ወይም የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ አለበቸው።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው
  7. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ አሪጅናሉንና ኮፒው ላይ በእያንዳንዱ ገፆች የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማኖር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ በሰነዱ ላይ ችግር ቢፈጠር /ቤቱ ተጠያቂ መሆን አይችልም፡፡
  9. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው
  10. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርግ ባቀረበው ናሙና መሰረት የማምጣት ግዴታ አለቸው፡፡
  11. አነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት በግዢና ንብረት አስተዳደር ህግ መሰረት የተቋቋሙበትን ህጋዊነት ማስረጃ ካደራጃቸው ተቋም ደብደቤ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  12. ፍያ የሚፈፀመው ሙሉ በሙሉ ለባለበጀት መሰሪያ ቤቶች ሲያስረከቡ እና የቀረበው እቃ ጥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 21 (ሃያ አንድ) የስራ ቀን በመቆየት 21 ኛው ቀን 1130 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከስራ ቀን ውጪ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ወይም (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ ማቅረብ ካልቻሉ ለሁለተኛ ተወዳዳሪ አሸናፊ የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. አሸናፊ የሆነ ድርጅት የአሸነፈበትን ዕቃዎች የማስጫኛና የማስወረጃ ወጪ እንዲሁም የትራንስፖርት በራሱ ሸፍኖ ማቅረብ አለበት።
  16. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09-17-01-68-99 ደውለው ይጠይቁ።

 

በኦ//አስ/ በጅማ ዞን የኦሞ ናዳ ወረዳ ገንዘብ /ቤት

 

Save Tender