የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን ነገሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን
ሎት 1 :- የጽህፈት መሳሪያዎች እና የፎቶ ኮፒ የፕሪንተር ቀለሞች ለመግዛት፤
ሎት 2 :- የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት፣
ሎት 3 :- የጽዳት እቃዎች ለመግዛት፤
ሎት 4 :- የኤሌክትሪክ፣ የቧንቧ፣ የግንባታ እቃዎች ለመግዛት፣
ሎት 5 ፡- የመኪና ጎማዎች ለመግዛት፣
ሎት 6፡- የመኪና ኪራይ ለ2018 በጀት አመት፣
ሉት 7 :- የተለያዩ የችግኝ ዝግጅት ግብአቶች እና እቃዎች ለመግዛት፣
ሎት 8 :- የባነር እና የብሮሸር ህትመት እና የተለያዩ ህትመቶች ለአንድ አመት ውል በማሰር ለማሰራት፣
ሎት 9 ፡- የአትክልትና ፍራፍሬ ለአንድ አመት ውል በማሰር ለመግዛት፤
ሉት 10 ፡- የሆቴል ምግብና መጠጥ አቅርቦት አገልግሎት የአንድ አመት ውል በማሰር ለመግዛት፣
ሎት 11 :- የበሬ ስጋ አቅርቦት ለአንድ አመት ውል በማሰር ለመግዛት፣
ሎት 12 :- ፋውንቴኖችን ፣የውሃ ፓምፖችን ፣ የጀኔሬተር፣ የሳር ማጨጃ ማሽን ውል በማሰር ሰርቪስ የማድረግ ስራ ለማሰራት፣
ሎት 13፡- በኮርፖሬሽኑ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ህንጻዎችና ፣ የቢሮ እቃዎች እና መጫወቻዎች የጥገና ስራ ውል በማሰር ለማሰራት፣
ሎት 14፡- ለእንስሳት መድሀኒቶች ቋሚ እቃዎች ለመግዛት፣
ሉት 15- የስብሰባ አዳራሽ ጠረጴዛ ለመግዛት፣
ሎት 16፡- የጉልበት ስራ ለአንድ አመት ውል በማሰር ለማሰራት፣
ሎት 17፡- የኮምፒዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ለአንድ አመት ውል በማሰር ለማሰራት ፣
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቶች ተጋብዘዋል።
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ (clearance) ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች ሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ መገኛኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻ እና ቴክኒካል ዶክመንት ለብቻ በማሸግ እና ሁለቱንም ለየብቻ ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኋላ 11ኛው ቀን ከሰአት 8፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 መገኛኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ስድስተኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0703229872 / 251777619010 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን
