በባሌ ዞን የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች ፤የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፕላስቲክ መገጣጠሚያዎች፣ GI መገጣጠሚያዎች፣ ሞተር ሳይክል፣ Calcium Hypho chloride (ክሎሪን)፣ ጎማዎችና መለዋወጫ፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
በባሌ ዞን የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፕላስቲክ መገጣጠሚያዎች፣ GI መገጣጠሚያዎች፣ ሞተር ሳይክል፣ Calcium Hypho chloride (ክሎሪን)፣ ጎማዎችና መለዋወጫ፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል በተሰማራበት ዘርፍ ህጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው።
- ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ የሚያቀርብ ተጫራች የውሃ ፈንድ ክፍያ 0.5 % መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል ከሮቤ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውና ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 2% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጨረታው ሰነድ በተጠቀሰው መሰረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በሙሉ የመጫኛና የማጓጓዣ ወጪውን በመቻል መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- የእቃዎቹን ዋጋ መስሪያ ቤቱ የሚከፍለው ተጫራቹ ለማቅረብ ውል የፈረሙባቸውን እቃ ሙሉ በሙሉ በንብረት ክፍላችን ገቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ሲቀርብ ነው።
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው በ3 ቀን ውስጥ መ/ቤት ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0966696974፣ 0904449498 ደውለው መጠየቅ ይቻላል ፡፡
የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
