Tender Detail

Tender Details


የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰዉ የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች፣ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ መዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ (YAMAHA Digital key bord)፣ የሞተር ሣይክል መለዋወጫዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ሣይክሎች እና የከብቶች መኖ (ፉርሽካ) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 11/2018

 

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን //ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰዉ የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች፣ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ መዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ (YAMAHA Digital key bord) የሞተር ሣይክል መለዋወጫዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ሣይክሎች እና የከብቶች መኖ (ፉርሽካ) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል። ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
  2. ማንኛውም የሞተር ሣይክል ተጫራች ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው ኢትዮጵያዊ መታወቂያ በማቅረብ መጫረት ይችላል።
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 200 እስከ 600 ከሰዓት 700 እስከ 1100 ሰዓት ቅዳሜ 200 እስከ 600 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጫራቹ ስም የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ//ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 6ኛው (ስድስተኛው) ቀን ግልፅ ጨረታው ጠዋት 400 ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ይካሄዳል። ነገር ግን የጨረታው ቀን እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይካሄዳል።
  6. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም።
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፣
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
  9. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
  10. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ቅሬታ ቢፈጠር //ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  11. ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።
  12. አሸናፊዉ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ//ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል።
  13. //ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 0462125396 ደውለው ይጠይቁ።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ //ቤት

 

Save Tender