በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ለቢሮ አገልግሎት እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፈው መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ለቢሮ አገልግሎት እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፈው መግዛት ይፈልጋል፡፡
ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018
- የቢሮ ዕቃዎች ሎት 1
- የደንብ ልብስ ሎት 2
- የመኪና የተለየዩ ዕቃዎች ሎት 3
- የኤሌክትሮኒክስ ሎት 4
- የህትመት ሎት 5
- የጥገና የኮምፒዩተር ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን እና ፈርኒቸር ጥገና ሎት 6
- ማስዋቢያ ሎት 7
- ዲኮር ሎት 8
- መስተንግዶ ሎት 9
- የፓርቲሸ ሎት 10
- የህፃናት መቆያ ዕቃዎች ሎት 11
- የጉልበት ስራ ሎት 12
❖ በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ ቲን ነበር ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 7ኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ፤
- የሚያቀርቡት እቃ ዋጋ ከብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጀ ከሆነ ቲእቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወቀረት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በጨረታ ላይ ያወጣናቸው እቃዎች በሙሉ ኦርጅናል እና ጥራቱን የጠበቀ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለተወዳደሩበት ዕቃ ልዩ ሳምፕል የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ያሸነፉዋቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤት ድረስ ማምጣት አለባቸው፣
- ተጫራቾች ለገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫት በመጨመር በስም የታሸጉ ኤንቨሎፕ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 7ኛ ፎቅ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ወይም በሚያቀርቡት እቃዎች ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ውል የተገባባቸውን እቃዎች በአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ከቢሮው የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የውል ስምምነት መፈጻም ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፣
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣
❖ አድራሻ፡- ሃያ ሁለት በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አለፍ ብሎ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቀረባቸሁ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111562305 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
