በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው 2018/2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ና የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ገንዘብ ሚኒስቴር በወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- አሸናፊ ድርጅት ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በአሥር ቀን ውስጥ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በሙሉ ኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በሥራ ሰዓት እስከ 11፡30 ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 1000 ብር (አንድ ሺህ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000036504416 በመክፈል ስሊፕ ለኩዩ ወረዳ ገቢዎች ቢሮ በማስገባት በማወራረድ ሰነዱን ከኩዩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ የያዘ ዝርዝር የዋጋ ሰነድ በፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) CPO በባንክ የተረጋገጠ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለበት፡፡ ማስከበሪያውን ካላስገባ (ካለስያዘ) ፖስታው አይከፈትም፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- በሌላ ሰው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የሥራ ልምድ እና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል፡፡
- መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በ2018 ዓ/ም በጽ/ቤታችን ተወዳድራችሁ ከአሸነፋቹ በኋላ ያሸነፋቹትን ዕቃዎችን ስምምነት በመግባት እንዲታቀርቡ ቢነገረችሁም ፍቃደኛ ያልሆናችሁና ያላቀረባችሁ ዘንድሮ የማናስተናግዳችሁና የማናወዳድራችሁ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0935971038/0911775600 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of office supplies, cleaning materials, furniture, electronics, vehicle tires, and staff uniforms for sector offices under Kuyu District Finance Office, North Shewa Zone, Oromia. Bidders must hold a renewed trade license, pay current taxes, and be registered with the Ministry of Finance supplier list.
