በቡኖ በደሌ ዞን የቦረቻ የወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልላዊ የመንግሥት ግዢ አዋጅ ቁጥር 157/2002 ዓ.ም መሰረት ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በቡኖ በደሌ ዞን የቦረቻ የወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልላዊ የመንግሥት ግዢ አዋጅ ቁጥር 157/2002 ዓ.ም መሰረት፡-
- የተለያዩ ብትን ጨርቃ ጨርቆችና የተዘጋጁ የደንብ አልባሳት፤
- እስቴሽነሪና አላቂ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች፤
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፤
- ቋሚ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች /ፈርኒቸር/
- የተለያዩ የህትመት ስራዎች፤
- የተለያዩ የመኪናና ሞተር ሳይክል ጎማና ካላማዳሪያ፤
- የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች፤
- የተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለዚሁም የሚያስፈልጉ መስፈርቶች-
- ከላይ የተዘረዘሩ የግዢ አይነቶች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያደሱ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 /አምስት ሺህ/ በሲፒኦ ወይም በካሽ ማስያዝ የሚችሉ፤
- VAT NO ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
- TIN NO ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
- በአቅራቢነት ዝርዝር መዝገብ ላይ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
- ናሙና ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተወዳድሮ ያሸነፈውን ዕቃ ሁሉ እስከ ቦረቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጠቀሱትን ዕቃዎች ሁሉ ኦሪጅናል የሆነ ማቅረብ የሚችሉና ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ነጋዴ ይህ ማስታወቂያ ወጥቶ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት መሀከል ቦረቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በማንኛውም የመንግሥት የስራ ሰዓት በማቅረብ ለዚሁ ዕቃ እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አድርገው ቦረቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በማምጣት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በማስገባት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ይህ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ የሚሸጥ በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ የሚሸጥና በዚሁ በተጠቀሰው ቀን መሀል ተሞልቶ የሚመለስ መሆኑን እየገለፅን በቦረቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት 16ኛ /አስራ ስድስተኛ/ የስራ ቀን ላይ ቢሮ ቁጥር 8 /ስምንት/ ውስጥ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ3፡30 ላይ ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሁሉም ትክክለኛ ማስረጃ ስለመሆኑ የሚገልጽ ኦሪጅናልና ኮፒው በተለያዩ ፖስታዎች ታሽጎ ሁለቱም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ታሽጎ መገኘት አለበት፡፡
- የዕቃው ዋጋ መቅረቢያ ዝርዝር በሌላ ፖስታ ታሽጎ መግባት ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች መካካል አንድ አንኳን ቢጎድል ፖስታው/ ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በውስጡ የሌለውን ማስረጃ አቀርባለሁ ወይም በእጄ ይዣለሁ የሚል ሰበብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ በቂ ምከንያት ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-45-02-02-36 ደውለው መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በቡኖ በደሴ ዞን የቦረቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
