Tender Detail

Tender Details


የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ 001/2018

 

የለሚ ኩራ ፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ /ቤት 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚመለከታቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

ሎት1. የደንብ ልብስ፣ ሎት2. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ ሎት3. የፅዳት ዕቃዎች ሎት4. የፕላንት ማሽነሪና ለመሣሪያ ኤሌክትሮኒ መግዣ ሎት5. የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሎት6. የህትመት ስራዎች፣ ሎት7. ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ሎት8. የመስተንግዶ ሎት9. የልብስ ስፌት፣ ሎት 10. ለፕላንት ማሸነሪ/ኤሌክትሮኒ /ጥገና ሎት11. የፈርኒቸር ጥገና፣ ሎት12. የኪራይ ዕቃዎች ሎት13. የመኪና ጎማ እና የመኪና እቃዎች፣ ሎት14.  የጉልበት ስራ በጨረታ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃቸውንና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስ ወረቀትና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
  2. ተጨማሪ እሴት ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት1. የደንብ ልብስ 10,000 /አስር ሺህ/ ብር፣ ሎት2. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ ብር፣ ሎት3. የፅዳት ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ ብር፣ ሎት4. ለፕላንት ማሸነሪና መሣሪያ /ኤሌክትሮኒ/ መግዣ 10,000 /አስር ሺህ/ ብር፣ ሎት5. የፈርኒቸር ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ብር፣ ሎት6. የህትመት ስራዎች 5.000 /አምስት ሺህ/ብር፣ ሎት7. ትራንስፖርት አገልግሎት 5,000 /አምስት ሺህ/ብር፣ ሎት 8. የመስተንግዶ 5,000 /አምስት ሺህ/ብር፣ ሎት 9. የልብስ ስፌት 2,000 /ሁለት ሺህ/ብር፣ ሎት10. ለፕላንት ማሸነሪ /ኤሌክትሮኒክስ/ ጥገና 2,000 /ሁለት ሺህ/ብር፣ ሎት11. የፈርኒቸር ጥገና 2,000 /ሁለት ሺህ/ብር፣ ሎት12. የኪራይ ዕቃዎች 5,000 /አምስት ሺህ/ብር፣ ሎት13. የመኪና ጎማ እና የመኪና እቃዎች ግዥ 5,000 /አምስት ሺህ/ብር ሎት14. የጉልበት ስራ ካደራጀቸው ወረዳ ደብዳቤ የቀረበ ዋስትና መሆን አለበት፡፡ ከሎት1 እስከ ሎት 13 ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እና በተባለው መሰረት በባንክ የተመሰከረለት /ሲፒኦ/ የተከፈለበት በአንዱ ከዋናው ዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
  4. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት እስከ ቀኑ አስራ አንድ /1100/ ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመፈል በለሚ ኩራ ፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ /ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 02 በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ ፖስታ ሰነዱን በኦርጂናልና ኮፒ በድርጅቱ ማህተም ማድረግና ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ጨረታው 10ኛው ቀን ከቀኑ 1100 ሰአት ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል፤ ስለዚህ ሁሉም ተጫራቾች ሰነዳቸውን አስገብተው ማጠናቀቅ አለባቸው
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ዋጋ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጂናልና ደረጃውን የጠበቀ ናሙና በጽ/ቤቱ ግዥ ቢሮ ማድረግ አለባቸው
  8. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ተወዳድረው ካሸነፋበት ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ክክለኛውን እቃ የማምጣት ግዴታ አለባቸው
  9. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ /ቤቱ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ሰአት በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% /C.P.O/ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. በማንኛውም ግልፅ ጨረታ ላይ ያልታገዱ መሆን አለበት፡፡
  12. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆን አለበት፡፡
  13. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሆነ የዋስትና ደብዳቤ ካደራጀቸው አካል በጽ/ቤት ኃላፊ በኩል ተፈርሞ የቀረበ ዋስትና መሆን አለበት፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ፕሮጀክት 15 ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ፡፡

 

ኩራ ክፍ ከተማ የወረዳ 06 ፋይናንስ /ቤት

 

Save Tender