የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀ/ል/ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2017
የግልፅ ጨረታ ዙር 01/17 በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀ/ል/ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥና አስተዳደር ቡድን ግዥ ግልፅ ጨረታ
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ
- ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 3 ኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 4 የተለያዩ ፈርኒቸርና የቢሮ ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 5 የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 6 የተለያዩ የመኪና አገልግሎት ኪራይ
- ሎት 7 የታሸገ ማዕድን ውሃ 0.6 ሊትርና የተዘጋጀ ቆሎ ግዥ
- ሎት 8 ልዩ ልዩ የህትመት ሥራዎች የአገልግሎት ግዥ
- ሎት9 መድረክ ማስዋብና የዲጄ መዝናኛ፣ የመድረክ መሪ፣ ኮፊ ሴሪሞኒና የድንኳን ኪራይ የቀን አገልግሎት ግዥ
- ሎት 10 የተሽከርካሪ የመኪና ባትሪ ድንጋይና የመኪና ልብስና ጌጣጌጥ የመኪና ጎማ ግዥ
- ሎት 11 የተለያዩ ሽልማት እቃዎች
- ሎት 12 የሠራተኞች የካፍቴሪያ ግብዓት ግዥ
በዚህም መሰረት ፡- በጨረታ ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ማሟላት የሚገባቸው
- የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና በሚወዳደሩበት መስክ ከንግድ ፈቃዱ ጀርባ ገላጭ መሆን አለበት፤ የግብር መክፈያ መለያ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ተጨማሪ 15% እሴት ታክስ ሰብሳቢ ምዝገባ፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር ቀጥታ ከዘርፉ ጋር የተጣጣመ ምዝገባ ኮፒ ሠርተፍኬቶች እንዲሁም ምግብ ነክ ለሆኑት በምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ወቅታዊ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው፣ የሚያቀርባቸው ማስረጃዎች ግልፅና ተነባቢ መሆን አለበት በእነዚህ ኮፒ ማስረጃዎች የድርጅትዎ ማህተም ከጀርባው ይደረግበት፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፍል ልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡ እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ የምትጫረቱ ተጫራቾች ሰነዱን የምታገኙት የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ነው።
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በመስሪያ ቤታችን ስም በልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊከ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥና አስተዳደር ቡድን ስም ሲፒአ አሰርተው ቴክኒካል አርጅናል ተበሎ በተሰየመው ፖስታ ማስገባት አለባቸው፡፡ ሲፒኦ ሲያሰሩ በሚወዳደሩበት በድርጅት ስም እንዲያስገቡ
- በሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 ሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 ሎት 6 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 ሎት 7 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 ሎት 8 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 ሎት 9 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 ሎት 10 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000 ሎት 11 የጨረታ ማስከበሪያ 40,000 ሎት 12 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 እየገለፅን ሎቶችን ጠቅልሎ ሲፒአ ማሰራት ከውድድር ውጪ ስለሚያደርግዎ ሲያሰሩ በእያንዳንዱ ሎት በመለየት ለየብቻ ሲፒአ ያሰሩ፡፡ በተጨማሪ የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ከሚመለከተው ተቋም ኦርጅናል ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ ከሰነዳቹ ጋር ማያያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ኢንቨሎፕ ሲያስገቡ የሚወዳደሩበትን የሎት ቁጥር መጥቀስና ፋይናንስ ከሆነ ፋይናንስ ኦርጅናልና ኮፒ፤ ቴክኒክ ከሆነ ቴክኒክ ኦርጅናልና ኮፒ፤ በማለት በሁለት ኤንቨሎፕ የሚከቱበት ፖስታ ላይ የሎት ቁጥሩንና ኦርጅናልና ኮፒ በመፃፍ እንዲያስገቡ እያሳሰብን ሲፒኦ ቴክኒካል ኦርጅናል ብለው በለዩት ፖስታ ውስጥ ይከተቱ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደራችሁበት ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ነገር ግን ቴክኒክ በሚለው ፖስታ ውስጥ የዋጋ ዝርዝር ሳይጨመርበት ሌሎች ተፈላጊ ማስረጃ መቅረብ ሲኖርበት ለሚወዳደሩ ቀጥተኛ ባለሙያና ብቃታቸውን የሚገልፅ ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋም ማስረጃ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም በመስክ ጉብኝት ጊዜ ለሚመለከታቸው ተባባሪ በመሆን ገለፃ ማድረግ ይጠበቃል።
- የጨረታው ሰነድ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ ቀኑ 11፡00 እንዲያስገቡ እያስታወስን በዕለቱ በ11፡00 የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን የመክፈቻው ቀን በ11ኛው ቀን ሲሆን ነገር ግን ቅዳሜና እሁድ ወይም በብሄራዊ በዓል አማካኝነት ዝግ ከሆነ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት 6ኛ ፎቅ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 605 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የተጫራች ወይም ወኪል አለመኖር ጨረታው ከመከፈት አያግደውም፡፡
- ከመስሪያ ቤታችን የዝዙት የጨረታ ሰነድ ውስጥ ክፍል 4 ላይ በተዘረዘሩት ላይ ዋጋ እንዲሞሉ እያሳሰብን ነገር ግን ከመ/ቤታችን ቅፅ ውጪ የሞሉት ሰነድ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም በሰነዱ ውስጥ ምንም አይነት ሌላ ፅሁፍ መፃፍ የለባቸውም።
- የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ፅሁፍ በእርሳስ የተፃፈ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ለግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ያቀርባል።
- መስሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ወይም የተመረጠ ተጫራች ተፈፃሚ የሚሆነው በውላቸው ስምምነት መሠረት ነው፡፡
ማስታወሻ፡- በጨረታው ተካፋይ ከሆኑ ተፈላጊ ሰነዶች ፖስታ ውስጥ ከመክተትዎ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመጀመሪያው ገፅ ላይ የሚገኘውን ማስታወሻ በትኩረት ይመልከቱ፡፡ ወይም ፐብሊከ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥና አስተዳደር ቡድን 6ኛ ፎቅ በአካል ቀርበው መረጃ ማግኘት ይችላሉ በተጨማሪ በስልክ ቁጥር 0118-55-25-49 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
አድራሻችን ፡- የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤትና አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ነው ልደታ ኮንዶሚኒየም በላይ ተክሉ አጠገብ የሚገኘው
የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤትና አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
