በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር የሚገኘው እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ቁጥር 001/18
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር የሚገኘው እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች
- የጽዳት ዕቃዎች የእንስሳ መኖ
- የጽህፈት መሳሪያዎች
- የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት
- የትምህርት ዕቃዎች መጽሐፎችና የስፖርት ዕቃዎች
- የተለያዩ የስጦታ ዕቃዎች
- የጥገና ዕቃዎች
- የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ኪራይ መኪና
- የእንስሳ ህክምና
- 60 ሰው መያዝ የሚችል ዘመናዊ አውቶቢስ ኪራይ
- የመኪና ዕቃዎች
- የማሽነሪ ዕቃ ጥገና እና ሰርቪስ
- ህትመት
- የህክምና ዕቃዎች ቋሚና አላቂ
- በት/ቤት ግቢ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የጥገና ሥራዎች
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ እና ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 103 መግዛት ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት 1ኛ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 111 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ጨረታው እስከሚከፈት ድረስ የዕቃ ናሙና መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው በሚያቀርባቸው ዕቃዎች ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 111 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ት/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ መሙያ ብቻ በመሙላት ማቅረብ እና ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ት/ቤቱ የሚገዛውን ዕቃ ብዛት 20% የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለሎት 1 እስከ 7 ብር 20,000.00 እና ለሎት 8፣9 እና 10 3,000.00 ለሎት 11፣12፣13 እና 14 20,000.00 ሎት 15 5,000 ባንክ የተረጋገጠ ክፍያ አቅርቦት (CPO) በፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩት በሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር ዕቃ ገዝተው የሚያቀርቡ ከሆነ እንደማንኛውም ተጫራቾች ሰነድ በመግዛትና ሲፒዮ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታ የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ (ማብራሪያ) ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0111261615 /0111 22 49 54/56 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የሚሰሯቸውን ስራዎች በሙሉ በአካል ት/ቤቱ በመገኘት ሳንፕል በመውሰድ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በአንድ የዕቃ አይነት በአንድ ብራንድ ብቻ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት ከ6 ኪሎ ዩንቨርሲቲ በግራ በኩል በሚወስደው መንገድ ወይም ምስካዬ ኅዙናን መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት
