የወላይታ ሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ለአንደኛ ዙር የተለያዩ የስልጠና ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የወላይታ ሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ለአንደኛ ዙር የተለያዩ የስልጠና ዕቃዎችን ማለትም፡-
ሆቴልና ቱሪዝም ዕቃ የቧንቧና ውሃ ሥራ ዕቃ
አግሮ ፕሮሰሲንግ ዕቃ የቅየሳ Seurveying/ ሥልጠና ዕቃ
ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ የከተማ ውበት /Urban greenery ዕቃ
አውቶሞቲቭ ዕቃ ቆዳና የቆዳ ውጤቶችን /ሌዘር
ማኑፋክቸሪንግ/ብረታ-ብረት ሳኒተሪ ዕቃዎች
እንጨትና የእንጨት ሥራ የቤትና ቢሮ/ፈርኒቸር ዕቃዎች
የአይሲቲ ኮምፒተር ዕቃዎች
የጽህፈት መሣርያዎች
የጽዳት ዕቃዎችን
ጋርመንት አልባሳት/ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ኮንስትራከሽንና ሮድ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይነት መለያ (VAT) ሰርተፍኬት ያለው፣
- በአቅራቢነት የተመዘገበበትን መረጃ/የድረ- ገጽ ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችል
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን የግብር ግዴታዎችን ስለመወጣታቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ማለትም፡-
- የእያንዳንዱን ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 104 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና ኮሌጁ ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ሞልተው በማስገባት መወዳደር ይቻላል፡፡
- ጨረታው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ2ኮፒ በጨረታ ሳጥኑ መጨመር ያለበት ሲሆን ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ የሚገዙ ድርጅቶች ሲፒኦን በጥቅል ማድረግ ሲችሉ ሌሎች ሰነዶችን በእያንዳንዱ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ካላሽጉ ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በማስላት በባንክ የተረጋገጠ ቼክ፤ ጋራንት እና ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጠቅላላ ዋጋ ከ1% በታች የሚያስገቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ፡፡ አሸናፊዎች በቅድሚያ 10% ውል በመግባት የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ውል ይገባሉ፡፡ አሸናፊ ድርጅቶች ውል ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆኑ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይደረጋል።
- ኮሌጁ ከአሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን ዕቃ የሚረከበው ውል ከገቡበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ ግቢ ብቻ ስለሆነ ጨረታውን የሚያሸንፉ ድርጅቶች ያሸነፉትን ሙሉ ዕቃ እስከ ኮሌጁ ግቢ በማምጣት የሚያስረከቡ ይሆናሉ። የዕቃዎቹም ጥራትና ዓይነት በኮሌጁ ባለሙያዎች ተረጋግጦ ተቀባይነት ካላገኘ ኮሌጁ ለመረከብ አይገደድም።
- ጨረታው የሚታሸግበት ቀንና ቦታ፡- ሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ሲሆን 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- የሚከፈትበት ቀንና ቦታ ወላይታ ሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በተጠናቀቀበት በ2ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተሸናፊ ድርጅቶች ያስያዙት ቼክና ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸውን ስፔስፒከሽን መቀየርና መደለዝ እንዲሁም የተደለዘ የተጫራች ሰነድ ተጫራቾችን ከጨረታው ውጪ ያደርጋቸዋል።
- ድርጅቶች ተገቢውን አድራሻ ማህተም ስልክ እና የፋክስ ቁጥርን ጨምሮ በሰነዱ መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0912111340 /0913302499/ 0916715114 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ወላይታ ሶዶ
