Tender Detail

Tender Details


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ማረ/ቤት ግ/ፋ/ን/ አስ/ቡድን ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል እቃዎች እና ለህግ ታራሚ ምግብና አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች መግዛት ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ማረ/ቤት /// አስ/ቡድን ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል እቃዎች እና ለህግ ታራሚ ምግብና አገልግሎት የሚውል

  1. ሎት -1 የእህል አቅርቦት የጨረታ ማስከበሪያ 80,000
  2. ሎት -2 የማገዶ እንጨት የጨረታ ማስከበሪያ 10,000
  3. ሎት -3 ሸቀጣ ሸቀጥ የጨረታ ማስከበሪያ 5,000
  4. ሎት -4 በርበሬ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000
  5. ሎት -5 ቅመማ ቅመም የጨረታ ማስከበሪያ 5,000
  6. ሎት -6 አትክልትና ፍራፍሬ የጨረታ ማስከበሪያ 5,000
  7. ሎት -7 ቋሚ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 15,000
  8. ሎት -8 የፅህፈት አላቂ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000
  9. ሎት -9 ጫማዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000
  10. ሎት -10 የቢሮ የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000
  11. ሎት -11 ህትመት የጨረታ ማስከበሪያ 5,000
  12. ሎት -12 ጨርቃ ጨርቅ የጨረታ ማስከበሪያ 5,000
  13. ሎት -13 ጎማና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 7,000
  14. ሎት -14 የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ 4,500

በመሆኑም ከሎት 1-14 ያሉትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች መግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ነምበር፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ሞልተው በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ የባለቤቶች ወይም የህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊርማና ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት።
  3. በየሎቱ የግዥ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታውን ቀርቦ የሚፈርመው ወኪሉ ከሆነ ህጋዊ የሆነ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ተወዳድረው የሚያሸንፏቸውን እቃዎች በራሱ ሙሉ ወጪ በመሸፈን በመ/ሜዳ /ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ በቁርጥ የተቀመጠውን ብር በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ያስያዙበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድርገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞሉትን ዋጋ ከተፈለገ መረጃዎች ጋር ማያያዝ አለባቸው።
  8. የጨረታ አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉን ሲገለጽለት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ባሉት ቀናቶች ውስጥ በጽ/ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ማስከበሪያ 10% /አስር በመቶኛ/ በማስያዝ ውል መፈጸም አለባቸው በጊዜ ገደቡ ውስጥ ቀርበው ውል ካፈጸሙ በግዥ መመሪያው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  10. የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ማድረግ አይቻልም፡፡
  11. አሸናፊው የሚመረጠው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ በተያያዘው ዝርዝር አትክልትና ፍራፍሬ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ ቅመማ ቅመም፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ቋሚ እቃ፣ የእህል አቅርቦት፣ በርበሬ፣ የማገዶ እንጨት፣ የጽህፈት አላቂ ዕቃዎች ህትመት፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ጎማና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች እና ጫማዎች እስፔስፊኬሽን መግለጫ በሚቀርበው ዝቅተኛ በሎት ድምር ወይም ነጠላ ዋጋ መሰረት ይሆናል።
  12. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ መመሪያ መሰረት በተታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።
  13. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆንላቸዋል።
  14. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 13/04/2018 እስከ 28/04/2018 . መሆኑን አውቃችሁ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው 28/04/2018 . 4:00 ሰዓት ታሽጎ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  15. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ///አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0116 851 539 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፣
  16. /ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በመ/ሜዳ ማረ/ቤት ///አስ ቡድን ስለሚገኝ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ኦርጅናል ሰነድ ላይ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
  18. ፖስታው የሚከፈትበት ቀን በዓላት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በዚያው ተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከታል፡፡
  19. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ማረ/ቤት

 

Save Tender